የዕንባ ጠባቂ ተቋም የዕንባ ጠባቂ ተቋም

የዕንባ ጠባቂ ተቋም ታሪካዊ አመጣጥ

ዕንባ ጠባቂ / Ombudsman/  መነሻው ስካንዲኔቪያን /Norse/ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንባ ጠባቂ ስራ  ላይ የዋለው እ.ኤ.አ.በ1809 በስዊዲን ሀገር ሲሆን “ተወካይ” (Representative) የሚለውን ሀሳብ ይገልጻል፡፡ ይህም አንድ ሰው ስሌላው በመሆን ችግሮችን ወደ መንግስት ወይም ወደ ባለስልጣን የሚያቀርብ መሆኑን ያመለክታል፡፡ስዊዲንን በመከተል ፊንላንድ እ.ኤ.አ በ1919፣ዴንማርክ በ1955፤ኒውዚላንድ በ1961፤ኖርዌይበ1963፤በአፍሪካ ታንዛኒያ በ1966፤በናሚቢያ በ1990፤በደቡብ አፍሪካ በ1995፤በኢትዮጵያ በ2000 እ.አ.አ.እንባ ጠባቂ ተቋም አቋቁመዋል፡፡ የዕንባ ጠባቂ ዓይነቶች ፓርላሜንታዊና ፓርላሜንታዊ ያልሆኑ በማለት በሁለት ሲከፈሉ በአሁኑ ጊዜ   በዓለም ላይ ከ140 በላይ በአፍሪካ ከ34 በላይ አገሮች ዕንባ ጠባቂ ተቋም አቋቁሟል፡፡

 የተለያዩ ጸሃፍት በተለያየ አይነት መልኩ ለዕንባ ጠባቂ ትርጉምና መግለጫ ይሰጣሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ዕንባ ጠባቂ በመንግስት ስልጣን ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚቀመጥ ግለሰብ ሲሆን ስራውም በአስተዳደሩ ላይ ወይም በሲቪል ሰራተኞች ላይ የሚቀርቡ የማንኛውም ዜጋ ቅሬታዎችን ተቀብሎ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚያደርግ ሲሆን ዕንባጠባቂ አቤቱታዎችን ተቀብሎ ተደጋጋሚ ስህተቶች ሲያጋጥሙት የህግ ወይም አሰራር  ማሻሻያዎች እንዲደረጉ፤ብልሹ አሰራሮች እንዳይቀጥሉ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡

የኦክስፎርድ መዝገብ ቃላት ደግሞ “ዕንባ ጠባቂን” እንደሚከተለው ይተረጉማል፡፡ ዕንባ ጠባቂ ማለት፡- “በመንግስት የተሾመ ባለስልጣን (ተሿሚ) ሲሆን ተግባሩም ዜጎች በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎች መርምሮ ሪፖርት ማቅረብ ነው፡፡ለዕንባ ጠባቂ የሚቀርቡ ቅሬታዎች/አቤቱታዎች ተቋማት በምን ያህል ጥራት ስራቸውን እያካሄዱ እንዳሉ ጠቋሚ መረጃዎች፡ግብረ-መልስ ሆኖ ሊገለግሉ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም የዕንባ ጠባቂ ትርጉሞች በአንድ ላይ ጠቅለል ባለመልኩ ስናስቀምጣቸው ዕንባጠባቂ የመንግስት ባለስልጣናት በዜጎች ላይ የአስተዳደር ጥፋቶችን ፈጽመው ዜጎች አቤቱታዎች ሲያቀርቡለት ቅሬታዎቻቸውን መርምሮ ሪፖርት የማቅረብ ስልጣን ያለው የህዝብ አገልጋይ ነው ማለት ይቻላል፡፡

የዕንባ ጠባቂዎች ዋነኛ አላማዎች በሁለት ትልልቅ ክፍሎች ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህም የህግ የበላይነትን በማስፈን ህጋዊነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ግልጸኝነትና በመንግስት ተቋማትና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ በማረጋገጥ መልካም የመንግስት አስተዳደርን /good administration/ መገንባትና ብልሹ አስተዳደርን /maladministration/ መከላከል ሲሆን ሌላው በመንግስት ተቋማትና በባለስልጣኖቻቸው ወይም በሰራተኞች አማካኝነት በደል በተፈጸመ ጊዜ ወይም ከብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ የዜጎች አቤቱታዎችና ቅሬታዎችን መርምሮ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ማፈላለግ የሚሉ ናቸው፤፤ የዕንባ ጠባቂ     የቅሬታ አቀራረብ ሁኔታና የእንባ ጠባቂ የመመርመር የስልጣን  ገደብ በተለያዩ አገሮች እንደየአገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ የተለያየ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የአስተዳደር በደል የሚቀጩበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ፍትሀዊነት የጎደላቸው ውሳኔዎችና ትዕዛዞችበወቅቱ ማረም ወይም እንዳይደርሱ መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፤አስተዳደራዊ በደሎች የተፈረፀመባቻ ዜጎች ተጎድተው እንዳይቀሩ በቀላሉ ቅሬታቸውን የሚያሰሙበትና መፍትሄ የሚሹበት ተቋም የማግኘት ፍላጎታቸው መሟላት ያለበት በመሆኑ፤ሕግ አውጪው በሕዝብ ተወካይነቱ ሕግ አስፈፃሚው አካል ተግባሩን በህግ መሰረት የሚያከናውንና የሚሰጣቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች የዜጎችን መብቶች የማይጋፉ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፤ስለ ሕግ አውጪው ሆኖ አስተዳደራዊ በደል እንዳይደርስ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ በመሆን ከሚያገለግሉት ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነውን የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ማቋቋም ፤ስልጣንና  ተግባሩን በህግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ.ኢ.ፌ.ዴ.ሪ   ህገ-መንግስት መሰረት የኢትዮጵያ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ጠቋም ስልጣኑና ተግባሩ ተወስኖለት በአዋጅ ቁጥር 211/1192 ተቋቁሞ  ተግባርና ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡