Asset Publisher Asset Publisher

አዋጅ 590/2000

አዋጅ 590/2000 ሀላፊነትና ግዴታ ከተጣለበችው የባለድረሻ አካላት ጋር የመረጃ ነፃነት አዋጁን በመፈፀም ረገድ በሚስታዋሉ ችግሮችና የመፍትሔ ሃሳቦች ዙሪያ በመወያየት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተቋማዊ በሆነ መልኩ መፍታት ይገባል፡፡ የዜጎችን የሃሳብና የአመልካከት ነፃነትን ተግባራዊ ለማድረግ ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ቅንጀታዊ ትብብር የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከፌደራል የመንግስት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት፣ ከክልል የመንግስት ኮሙኒኬሸን ቢሮ ጋር ለመስራት ስምምነት ተደረሷል ፡፡
የመረጃ ነፃነት ህጉን ለማስተግበር የሦስቱ አስተግባሪ አካላት ሀላፊነት
//////////////////////
1. የፌደራል መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ተግባርና ሃላፊት
• በፌደራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ መንግሥታዊ አካላትና ተጠሪ መ/ቤቶች ለመረጃ ነጻነት ትግበራ ለየመሥሪያ ቤቶቻቸው ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የሰው ሐይልና በጀት እንዲመድቡና እንዲያጠናክሩ ማበረታታት፣
• የእያንዳንዱ መንግሥታዊ አካል የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ፡-
• የመረጃ ነጻነት አዋጁ በሚያዘው አግባበብ የመረጃ ነጻነትን ተግባራዊ ስለማድረጉ መከታተልና መደገፍ፣
• የመረጃ ነጻነት አዋጅን ለማስፈጸም ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እንዲያቀርብ ግፊት ማድረግ፣
2. የክልል መንግሥታት እና የከተማ አስተዳደሮች የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ቢሮዎች የሥራ ድርሻ/ሃላፊነት
• በክልላዊ መንግሥቱ ሥር የሚገኙ መንግሥታዊ አካላትና ተጠሪ መ/ቤቶች ለመረጃ ነጻነት ትግበራ ለየመሥሪያ ቤቶቻቸው ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የሰው ሐይልና በጀት እንዲመድቡና እንዲያጠናክሩማበረታታት፣
• በክልሉ የሚገኝ የእያንዳንዱ መንግሥታዊ አካል የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ፡-
• የመረጃ ነጻነት አዋጁ በሚያዘው አግባበብ የመረጃ ነጻነትን ተግባራዊ ስለማድረጉ መከታተልና መደገፍ፣
• የመረጃ ነጻነት አዋጅን ለማስፈጸም ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እንዲያቀርብ ግፊት ማድረግ፣
3. የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሥራ ድርሻ
• በመረጃ ነጻነት አፈጻጸም ላይ የምክር፣የሥልጠናና የክትትል አገልግሎት መስጠት
• የመረጃ ነጻነት (አዋጅ ቁጥር 590/2000 ክፍል ሶስት) አንቀፅ 32 ሥልጣንና ተግባር መፈፀምና ማስፈፀም፤
• ከመንግሥታዊ አካላት የሚቀበለውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ በአፈጻጸማቸው ለተሻሉ መንግሥታዊ አካላት ምስጋናና እውቅና መስጠት
• በመረጃ ነጻነት ህጉ አግባብ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ መንግስታዊ አካላትን በመለየት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ለክልል ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረብ
• በምክክር መድረኩ የተገኙ መልክካም ተሞክሮዎችንና ሊታረሙ የሚገቡ ጉዳዮች በመለየት የአፈጻጸም ሪፖርት ለምክክር ጉባኤው የማቅረብ ሃላፊነት አለበት፡፡
• የባለድርሻ አካላቱ ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኙ የሀገራችንን የመረጃ ነፃነት አፈፃፀም ግምገማ ውጤቶች ላይ ተመስርቶ በወደፊት አቅጣጫ ላይ መወሰን እንዲቻል ማመቻቸት፡፡
4. የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች የህግ፣ ፍትሕ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሥራ ድርሻ/ሃላፊነት
• የየምክር ቤቶቹ የህግ፣ ፍትሕ እና የዲሞከራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመረጃ ነጻነትን አፈጻጸም አስመልክቶ በቼክ ሊስቶቻቸው በማካተት አፈጻጸሙን መከታተል ይጠበቅባቸዋል፣
• ሌሎች የምክር ቤቶቹ ቋሚ ኮሚቴዎች ለክትትልና ድጋፍ ስራ ወደ ክልል ሴክተር፣ ዞንና ወረዳ መ/ቤቶች በሚወጡበት ጊዜ የመረጃ ነጻነት አፈጻጸምን በቼክ ሊስታቸው እንዲያካትቱ ግፊት ማድረግ፣
• በየደረጃው የሚገኙ የክልል መንግስት አካላት የበላይ ሃላፊዎች ለየክልሉ ምክር ቤት እና ለየክልል አስተዳደር ምክር ቤት የመረጃ ነጻነትን ለማስፈጸም ያከናወናቸውን ተግባራት አመታዊ ሪፖርት ማቅረባቸውን ማረጋገጥ እና እንዲያቀርቡ ክትትል ማድረግ እና
• ለመረጃ ነጻነት ትግበራ እንቅፋት የሆኑና ተጠይቀውም ሆነ ሳይጠየቁ መረጃ በማይሰጡ የመንግሥት አካላት የበላይ ሃላፊዎች ላይ ትክክለኛ ማስረጃ ሲቀርብ ተገቢውና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለተከበረው ምክር ቤት ምክረ ሐሳብ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

 

 
 
 
 
You and 27 others
 
 
6 Shares
 
Like
 
 
 
Comment
 
 
Share